Saturday 13 December 2014

ኢትዮጵያዊነት: አሰባሳቢ ማንነት

ሃሰን ዑመር አብደላ በሚል የብዕር ስም ጦቢያ መጽሔት ላይ ይጽፉ የነበሩ አቶ ዩሱፍ ያሲን ”አሰባሳቢ ማንነት ባንድ ሃገር ልጅነት፣የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ” በሚል ርዕስ ያዘጋጁትን መጽሐፍ ከሦስት ሳምንት በፊት የኦስሎ ነዋሪዎች ባዘጋጁት ፕሮግራም ላይ አስመርቀዋል:: በወቅቱም ከኦስሎና አካባቢዋ እንዲሁም ከሌሎች የአውሮፓ ሃገራት የመጡ ኢትዮጵያውያን በብዛት ተገኝተዋል:: ሰዓት አልበቃ እስኪል ድረስ ሞቅ ደመቅ ያሉ ውይይቶች መጽሐፉን በተመለከተ ተካሂደዋል:: ጥያቄዎችና ትችቶች ተነስተዋል:: ምስጋናዎችና አድናቆቶችም እንዲሁ:: ለተነሱ ወሳኝ መስለው ለታዩ ጉዳዮች ጸሐፊው አጠር አጠር ያሉ ግን ሞቅ ደመቅ ያሉ መልሶችንና እይታዎችን አቅርበዋል:: የጋለውን ውይይት ከተመለከቱ በኋላም መጽሐፉ ከአሁኑ ዓላማውን እየመታ እንደሆነ ተናግረዋል:: ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉም የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ውይይቱን አጠናክሮ  እንዲቀጥልና መግባባት ላይ እንዲደርስ አጠንክረው አሳስበዋል:: 

Saturday 29 November 2014

ምን አይነት ሰላማዊ ሰልፍ?

ለመጀመሪያ ጊዜ በሰላማዊ ሰልፍ የተሳተፍኩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 ኪሎ ግቢ ተማሪ እያለሁ ነበር:: በአራት ዓመት የትምህርት ቆይታዬ በርከት ያሉ ሰልፎች ተካሂደዋል:: አንዳንዴ የምግብ ጥራት ማሽቆልቆሉን በመቃወም ሌላ ጊዜ ነጻነትን ፍትህንና ዴሞክራሲን እንዲሁም የመሬት ክፍፍልን በመቃወም:: ምግብን በተመለከተ የተቀናጁ ሰልፎች አጀማመራቸው ምግብ-ነክ ይሁን እንጅ መደምደሚያቸው ፖለቲካ ነበር:: ድንገት ከሰልፉ መካከል አንዱ ተነስቶ "ፍትህና መብት ይከበር" ካለ ተሜ ወዲያው ተቀብሎ  ያስተጋባዋል:: አንዳንዶች ደግሞ በራሳቸው ተነሳሽነት ቀድሞ የተዘጋጀ የጽሁፍ መፈክር ብቅ ያደርጋሉ:: በአቅራቢያቸው ያለ ተሜ እያነበበ ያስተጋባዋል:: ሌላው ይቀበለዋል:: የአንገት ስር እስኪወደር ድረስ ይፎከራል:: ስሜት እየጋለ ይሄዳል:: የተሰላፊው ቁጥር የሚጨምረው ሰልፉ ከተጀመረ ከበርካታ ደቂቃዎች በኋላ ነው:: መጀመሪያ ላይ ፈራ ተባ እያሉ ከዳር ሆነው የሚመለከቱ  ይበዛሉ.: በኋላ ድንገት ሰልፉን የሚቀላቀሉ ይበዛሉ:: 


Friday 17 October 2014

ፓትርያርክ ብፁዕ አባ ማትያስና ተግዳሮቶቻቸው

ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከተሾሙ እነሆ ሁለት ዓመት ሊሞላቸው አራት ወራት ገደማ ይቀራቸዋል:: ቅድመና ድኅረ ሹመታቸውን ተከትሎ የውይይትና የክርክር መድረኮች በኢትዮጵያም በውጭውም ዓለም ተከፍተው ነበር:: የአምስተኛው ፓትርያርክ የብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ድንገተኛ ሞት አንዳች ለውጥ ለቤተ ክርስቲያኗ ያመጣ ይሆናል ብለው የገመቱና የተመኙ ብዙዎች ነበሩ:: ሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ ሊያወርዱ እንደሚችሉ ተተነተነ:: ዳሩ ግን የእርቁ ሂደት ሳያልቅ ምርጫ ተደረገና ብፁዕ አቡነ ማትያስ በወሳኝ ድምጽ እንዳሸነፉ ተነገረ:: በዚህም የመንግስት ጫናና ማስፈራራት እንደነበረበት ተወሳ:: እርሳቸውም ነጭ ልብስ እንደማይለብሱና የቅንጦት ኑሮ እንደሚጸየፉ: ቤተ ክርስቲያን ያጣችውን ክብርና ተሰሚነት እንደሚመልሱ ተናገሩ:: «ይህን ማን አየው» በሚል ተስፋ አዲሱ ፓትርያርክ የለውጥ ሐዋርያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ቅር እያላቸውም ቢሆን የገመቱ ነበሩ::

Wednesday 10 September 2014

አዲሱ ዓመትና ተፈላጊው ኢትዮጵያዊነት

ኢትዮጵያ ካሏት ብርቅዬ እሴቶች ውስጥ የዘመን አቆጣጠር ሥርዓቷና ተያይዘው የሚከናወኑት ተግባራት ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ናቸው:: አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓላማና ተስፋ በመሰነቅ በደመቀ ሁኔታ ያከብሩታል:: የተሻለ ለመስራት ቃል ይገባሉ:: ከአጉል ልምዶችና ከጎጅ ስብዕና ለመላቀቅ እቅድ ይነድፋሉ:: ዳሩ ግን ብዙውን ጊዜ እቅዶች የግል ህይወትን ማለትም ሥራን: ትዳርን: ቤተሰብን: ትምህርትንና ጤናን የተመለከቱ ናቸው:: ሰብአዊ: ህገ መንግስታዊና ተፈጥሮአዊ መብቶቻቸው ሲጣሱ ከማየትና በር ዘግቶ ከማማት በስተቀር በእቅድ ይዘው ለውጥ ለማምጣት ሲጥሩ የሚታዩ እምብዛም ናቸው:: በአዲስ ዓመት ራሳችንን ከማንኛውም አላስፈላጊ ጫና ነጻ ለማውጣት ስናቅድ አንታይም:: ይህም አምባና ብሄር ገነንነት ተጠናክሮ  እንዲቀጥል የራሱን ድርሻ እያደረገ ነው::

Thursday 7 August 2014

ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ለኢትዮጵያ: ጥናታዊ ጽሁፍ

በአገራችን ኢትዮጵያ ያለውን ብሄር ገነን ሥርዓት በእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ለመተካት ኢትዮጵያውያን (የ አገር ዜግነት ያላቸውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንንም ማለቴ ነው) የተለያዩ  መንገዶችንና ዘዴዎችን በመጠቀም እየታገሉ ይገኛሉ:: በአገር ቤት ያሉ ወደ 100 የሚጠጉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በይፋ ሰላማዊ የትግል ስልት ይከተላሉ ቀላል የማይባል ህዝብም በሰላማዊ መንገድ መታገል እንደሚበጅ ያምናል:: በጣት የሚቆጠሩ ድርጅቶች ደግሞ እሾህን በእሾህ እንዲሉ መሳርያ አንስተው ወደበረሃ ገብተዋል:: እንደ ግንቦት 7 ያሉት ደግሞ ሁሉንም አይነት የትግል ስልት መጠቀም አዋጭ እንደሆነ ያምናሉ::

Wednesday 6 August 2014

ሰላማዊ ሕዝባዊ ትግል!


ሰላማዊ ትግልን አልፎ  አልፎ  በሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍና በየአምስት ዓመቱ በሚመጣ ምርጫ መሳተፍ የምንወስነው ከሆነ ይህ የትግል ስልት ውጤት የለውም:: ዳሩ ግን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች እንደሚነግሩን ሰላማዊ ትግል እጅግ ሰፊ ግን ተደጋጋፊ ስልቶችን ያካትታል:: ይህ ከግምት ውስጥ ሲገባ ወደ አንድ ድምዳሜ ይወስደናል:: ሰላማዊ ህዝባዊ ትግል በኢትዮጵያ አንዱዓለም አራጌ እንደገለጸው ገና ያልተሄደበት መንገድ ነው:: እስካሁን ፖለቲካዊ ለውጥ ያልመጣው አማራጭ የሰላማዊ ትግል ስልቶች ተቀነባብረውና በቀጣይነት ሥራ ላይ ስላልዋሉ ነው::

Saturday 12 July 2014

አገራዊ ስሜት ለምን ይጎድለናል? የመጨረሻ ክፍል

አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ቀዝቃዛ ስሜት እንዳለውና በቂ ተሳትፎ እንደማያደርግ በመደምደም የችግሩን መንስኤዎች ወይም ምክንያቶች በተከታታይ ጽሁፎች ማቅረብ ጀምሬአለሁ:: ክፍል አንድ አገራዊ ስሚት ምን ማለት እንደሆነ ካብራራ በኋላ ብዙው ኢትዮጵያዊ በብሄራዊ ጉዳዮች የመሳተፍ ዝንባሌና ፍላጎት እንዲሁም ሥነ-ልቡናዊ አቅም እንደሌለው አትቷል:: ክፍል ሁለት ደግሞ ባህላዊ አስተምህሮቶቻችን ፖለቲካዊ አገራዊ ጉዳዮችን በንቃት እንዳንከታተል ተጽዕኖ እንዳደረጉብን አብራርቷል:: እንዲሁም ብዙ ሰዎች ተሳትፎ ቢያደርጉ መንግስት በህይወታቸው: በቤተሰባቸውና በሥራቸው ላይ መከራ እንደሚያመጣባቸው በማመን "ዝምታ ወርቅ ነው"ን እያዜሙ እንደሚኖሩ አትቷል:: በዚህ የመጨረሻ ክፍል ደግሞ  ስለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዳዮች የበኩላችንን አስተዋጽዖ እንዳናደርግ ያደረጉንን ሌሎች እንቅፋቶች ለመዘርዘር እሞክራለሁ:: 

Saturday 7 June 2014

አገራዊ ስሜት ለምን ይጎድለናል? ክፍል 2

በክፍል አንድ ጽሁፌ ብዙ ኢትዮጵያዊ በቂ የአገር ስሜት እንደሌለው ሞግቻለሁ:: አገራዊ ስሜት ማለትም አገራችንን በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮችን በነቃ አእምሮ ተከታትሎና መርምሮ የራስን ግንዛቤ መውሰድ ከዚያም የሚገባውን አስተዋጽዖ ማድረግ እንደሆነም ጠቁሜአለሁ:: በስብሰባዎችና የውይይት መድረኮች መሳተፍ: የፖለቲካ ወይም የሲቪል ተቋማትን መምራት ወይም አባል መሆን: የራሱና የሌላ ሰው መብት ሲጣስ መቃወም: እድገትና ለውጥ በሚያመጡ ፕሮጄክቶች መሳተፍ ወዘተ የአገራዊ ፖለቲካዊ ስሜት የሚገለጥባቸው መንገዶች እንደሆኑም ለምሳሌነት አንስቻለሁ:: ከዚያም አገራዊ ጉዳዮችን በአንክሮ እንዳንከታተልና በሚገባ እንዳንሳተፍ የሚያደርጉ መንስኤዎችንና ምክንያቶችን በዝርዝር ማንሳትና መወያየት ፖለቲካዊ ንቃተ ኅሊናን ለማሳደግ በሚደረግ ጥረት አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ አሳስቤአለሁ:: በዚህ ጽሁፍ ሁለት ለአገራዊ ስሜት በበቂ ሁኔታ አለመኖር ተጠቃሽ መንስኤዎችን ወይም ምክንያቶችን ለውይይት አቅርቤአለሁ::   

Friday 6 June 2014

D-Day: The Ethiopian Type!

Today, June 6, marks the 70th anniversary of the D-Day. Celebrations and commemorations are underway at  Normandy, France. In October 2013, I wrote a piece on Ethiopian politics, see below, by taking into consideration the concept of the D-Day. It was read by 4, 000 people from North America to Europe to Africa including Ethiopia.  I feel the points raised are still relevant and significant to all who gets involved in Ethiopian politics. Have a good read! 

Friday 30 May 2014

አገራዊ ስሜት ለምን ይጎድለናል

ከበርካታ ሳምንታት በፊት ከጓደኞቼ ጋር ኢትዮጵያ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ እየተወያየን ነበር:: ሁሉም ተሳታፊ የተስማማበት ጉዳይ ቢኖር ኢትዮጵያ ከምንም ጊዜ በላይ እጅግ ከባድ ማኅበራዊ ምጣኔ ሃብታዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ መግባቷን ነበር:: ለዚህም በግንባር ቀደምነት ተጠያቂው መንግስት እንደሆነ ቢሰመርበትም ህዝቡም ላለንበት ሁኔታ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ታላቅ አስተዋጽዖ እያደረገ እንደሚገኝ ተወስቷል::

Friday 14 March 2014

ብአዴንንም ጠበቅ!

              
ኢሕአዴግን እንደመሰረቱ ከሚነገረው አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ኢትዮጵያን በአንደኛ ደረጃ የጎዳ ወይም ያዳከመ የትኛው ነው ብለው ያስባሉ? ለምን? ለዚህ ጥያቄ ወጥ የሆነ መልስ ሊኖር አይችል ይሆናል:: እያንዳንዳችን ያለን አስተሳሰብና ፍልስፍና ሊለያይ ይችላልና:: ነገር ግን በመረጃ ተኮር የአስተሳሰብ ብሂል የሚጓዝ ማንኛውም ሰው ሊሰጠው የሚችለው መልስ ሊመሳሰል ይችላል:: ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ያለውን የአገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ መክተት ለምንሰጠው መልስ ጥሩ መነሻ ይሆናል::

Sunday 5 January 2014

ጎጂ ባህሎቻችን (የመጨረሻው ክፍል)

በዚህ የመጨረሻ ክፍል ከአስተሳሰባችንና ከአመለካከታችን ጋር ቀጥታዊ ግንኙነት አለው ብዬ የማስበውን ጎጂ ባህል አቀርባለሁ:: ይህን ጎጂ ባህል በሚገባ መመርመርና ማስወገድ ከቻልን አገራችን ኢትዮጵያ ከምትገኝበት ሁለንታዊ ችግሮችና ቀውሶች ለመላቀቅ የሚያስችላትን ትክክለኛ መንገድ ልትይዝ ትችላለች:: ቀጣይነት አስተማማኝና ሁሉን አቀፍ የሆነ የእድገታዊ ለውጥ መሰረት ሊጣል ይችላል:: ነገር ግን ይህን ጎጂ ባህል ተቋቁሞ ማለፍና ለቀጣይ ብሄራዊ ለውጥ መስራት ፈታኝ እንደሆነ ግልጽ መሆን አለበት:: ይህን ጎጂ ባህል አጠር አድርጌ ከገለጽኩ በኋላ መፍትሄ ጠቋሚ ሃሳቦች ላይ አተኩራለሁ::

Who will Win: Fano or the Government?

  The government's war for "disarmament" in the Amhara region has become much more   complicated than everyone’s expectation. ...