Posts

ሕዝባዊ ትግሉና ዲያስፖራው

ሕዝባዊ ትግል ወይም አመጽ ወሳኝ የትግል ስልት መሆን እንደሚችል ካለፉት ጥቂት ዓመታት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን እያካሄዱት ያሉት ትግል ጥሩ ማስረጃ ነው። ትግሉ እስካሁን ድረስ ከተገመተው በላይ በርካታ ድሎችን አስገኝቷል። ቀጥለው የተዘረዘሩትን ዋና ዋና ክስተቶች  የትግሉ ውጤት እንደሆኑ መናገር ይቻላል። አንደኛ መንግስት ሊተገብራቸው ያቀዳቸውን ፕሮጀክቶች ለጊዜውም ቢሆን በሕዝብ ትግል የተነሳ እንዲቆሙ አድርጓል። ሁለተኛ ትግሉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ አድርጓል። ሦስተኛ የክልል ባለ ሥልጣናት በተወሰነ መልኩ ሕወሓትን እንዲገዳደሩ የሞራል ተነሳሽነት ሰጥቷል።

ኢትዮጵያዊ የዐማራ ተጋድሎ

ከጥቂት ወራት ወዲህ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረ ከሳቡ ወሳኝ ጉዳዮች ውስጥ የዐማራ መደራጀት ዋናው ሳይሆን አልቀረም። ይህን ጉዳይ በተመለከተ በርካታ ጽሑፎችና ንግግሮች ተደርገዋል። ዐማራው እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነገድ መደራጀትና ራሱን ከተቀነባበረ ጥፋት ማዳን እንዳለበት የሚሞግቱ በርካቶች ናቸው። አሳማኝ የመከራከሪያ ነጥቦችንም አንስተዋል። በአንጻሩ ደግሞ ዐማራው በኢትዮጵያዊነት እንጅ በነገዱ መታገል መዘዙ ብዙ እንደሆነ ያስጠነቀቁ አሉ። ከሁለቱም ወገኖች አንዳንዶች ነጥቦቻቸውን በምክንያት ወይም በመረጃና በማስረጃ መደገፍ ሲሳናቸው አፍ አውጥተው ሌሎች ጸሐፍትን ሲሳደቡና «ወያኔ ነህ»«ጸረ ዐማራ ነህ»እያሉ ሲያሸማቅቁ ታይተዋል። ከነዚህ ከተሳዳቢዎችና ከአሸማቃቂዎች በስተቀር ለሌሎች ጸሐፍት ከፍ ያለ አክብሮትና ምሥጋና አቀርባለሁ። መሠረት ያላቸው ውይይቶችና ክርክሮች ለሚደረገው ትግል ግልጽነትንና    መናበብን ይፈጥራሉና!

Asrat Woldeyes & Ethiopian Politics

Image
September 1997. I was in Bichena, the stronghold of the hero Belay Zeleke. My plan was to reach at Addis Ababa University (AAU) for registration as a final year 
undergraduate student. Unfortunately, the scheduled bus failed to appear. Everyday 
around 6pm, we passengers were supposed to get registered afresh, hoping the bus 
could come the next day. We did registration six times, that is for six days. My 
money generously given by my relatives run real fast and I was in shock. But most 
worrisome was whether I could reach for the registration at AAU. Every passing day 
seriously touched my nerves. That time, no mobile, no Internet. It was real dark time.

የወቅቱ ፖለቲካዊ አሰላለፍና ፋይዳው

የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል እየሰፋና ቀጣይነቱን እያረጋገጠ ሲሄድ በውጭው ዓለም የሚገኙ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ባህርያቸውን ይበልጥ እየገለጡ መጥተዋል። ግለሰብ ተኮር እንቅስቃሴዎች ወደ ድርጅት ወይም ማኀበር ወይም ኅብረት እየተለወጡ ነው። ይበልጥ ትኩረት እየሳበ የመጣው ግን የድርጅቶቹ ብዛት ሳይሆን የተነሱበት ዓላማ ወይም ግብ ነው። የአንዳንዶች የትግል ባህርይ ከተጠበቀው በአንፃሩ ሆኖ በመገኘቱ ጥቂት በማይባሉ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ቁጣና ግርምትን ፈጥሯል። ይህን ተከትሎ ክርክሮችና ተግሳጾች በመገናኛ ብዙኃን እየወጡ ነው። እኒህ አይነት እንቅስቃሴዎች ትግሉ ምን ያህል ሰላማዊና አንድነትን የተላበሰ እንደሚሆን ካሁኑ ግርታን ፈጥረዋል።

ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ!

በአገራችንበኢትዮጵያያለውሁኔታእጅግአሳዛኝ፣አሳሳቢ፣አጓጊምሆኗል።ፈጣሪበኋላምዓለምአቀፍናብሄራዊሕግጋትየሰጧቸውንበፍጹምበነጻነትየመኖርመብታቸውእንዲከበርላቸውየጠየቁወገኖቻችንበመሰዋታቸው፣አካለስንኩላንበመሆናቸው፣የሲዖልአምሳያ

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር!

Image
ታሪካዊ የለውጥ ጎዳና ለኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በአገራችን እየተደረገ ያለው የሕዝብ ተቃውሞ አስፈላጊና አበረታች እንደሆነ ሞግቻለሁ።የትግሉም ዓላማ እውነተኛና ዘላቂ ዴሞክራሲና ነጻነት ማስፈን እንደሆነም ከሕዝቡ መፈክሮች በመነሳት አትቻለሁ።በተጨማሪም መንግስትና ደጋፊዎቹ፣ትግሉን በማካሄድ ላይ ያለው ሰፊው ሕዝብ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች፣የሃይማኖት ተቋማትና የመገናኛ ብዙኅን ይህን መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ልዩና ላቅ ያለ አስተዋጽዖ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁሜያለሁ። ሕዝቡ የትግሉ ባለቤትና ኦዲተር ሆኖ ሥራአሥፈጻሚ አካል ወይም ልዩ ብሄራዊ ኮሚቴመምረጥ እንዳለበትም ለማሳየት ሞክሬ ነበር።በመጨረሻም ኮሚቴው ለምንና እንዴት መመረጥ እንዳለበት ለመነሻ ያህል ጥቂት ነጥቦችንአንስቻለሁ።በዚህ ጽሑፍ ደግሞ ይህ ለውጥ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዴት እንደሚመረጥና የትግል መርሆቹና ስልቶቹ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ዘርዘር አድርጌ አቀርባለሁ።

ታሪካዊ የለውጥ ጎዳና ለኢትዮጵያ

Image
ኢትዮጵያዊያን እጅግ የተቀናጀ፣ ያመረረና ቀጣይነትም ያለው የሚመስል ተቃውሞ በመንግስት ላይ እያካሄዱ ይገኛሉ። ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሏል። የአዲስ አበባ የመስፋፋት እቅድና የመሬት ቅርምት እና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ቢያነሳሱትም መሠረታዊ የሆኑ የመብትና የነጻነት እንዲሁም የፍትህ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ትግሉ በሰላማዊ ሰልፍ ተጀምሮ ሁለ ገብ የሆኑ ስልቶችን ወደ መጠቀም የተሸጋገረ ይመስላል። በመቶዎች የሚቆጠሩት ሰልፈኞች በመንግስት ታጣቂዎች ተገለዋል፣ ቆስለዋል፣ ታስረዋል። ከመንግስት በኩልም ቁጥራቸው ያልታወቀ ወገኖች ሞተዋል፣ ቆስለዋል።  የታሰሩ ግን የሉም። ይህም ሁሉ መከራ ወርዶ ህዝቡ ለበለጠ ትግል ተነሳስቷል። እስካሁን የተከናወኑት ክስተቶች እንዲሁም ህዝቡ የሚያስተጋባቸው መፈክሮች በግልጽ እንደሚያሳዩት መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ በህዝቡ ዘንድ  ተቀባይነትን እንዳጣ ለመረዳት ችሏል። ለመሆኑ ህዝባዊ ትግሉ አስፈላጊ ነውን?